Commercial Nominees PLC

     ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ  

  Commercial Nomminees PLC

 

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/11/2013

 

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውል፡- 

ሎት 1:- 65% ፖሊስተር 35% ቪስኮስ ጨርቅ ካኪ ቀለም ብዛት 46,308 (ሱሪ፣ሸሚዝ እና ኮፍያ) እና ከረቫት    

        65% ፖሊስተር 35% ቪስኮስ ጨርቅ ጥቁር ሰማያዊ ቀለም ብዛ 46,308 እና 65% ፖሊስተር 35% 

        ቪስኮስ ጨርቅ ኦሞ ቀለም ብዛት 9,528 የጨርቅ አቅርቦት እና የስፌት አገልግሎት በአንድ ላይ 

        በሸሚዝ እና ኮፍያው ላይ በኢምብሮደሪ ሎጎ ይኖረዋል፤

ሎት 2:- የተለያዩ የጽዳት እቃዎች በማዕቀፍ ግ የሚፈጸም (ቪም፣ ፈሳሽሳሙና፣ መወልወያ፣ ፓምፕ ናይለን 

        መጥረጊያ ወ.ዘ.ተ.)

ሎት 3:- የተለያዩ የቢሮ መገልገለያ እቃዎች (ፈርኒቸሮች)፤

ሎት 4:- የተለያዩ የአይቲ እቃዎች (IT Equipments) የቅርንጫፍ ኔትወርክ ዝርጋታ፤ 

 

ከላይ የተዘረዘሩትን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ በማአቀፍ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ ለሎት 1 እና ለሎት2 የ3ዓመት የማዕቀፍ ግዢ ይሆናል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ቢትወደድ ባህሩ አብርሀም ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳዱ ሎት ብር100,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ቢትወደድ ባህሩ አብርሀም ህንፃ 3ኛ ፎቅ 

ስልክ ቁጥር 011-550 09 95

አዲስ አበባ 

ኢትዮጵያ





Posted Date:- May 12,2021